loading

አሜሪካ በዚምባቡየ ላይ የጣለችውን ማእቀብ  አራዘመች፡፡

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ዚምባቡየ ላይ ከአሁን ቀደም የጣለው ማእቀብ በአንድ ዓመት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

አሜሪካ ማእቀቡን ያራዘመችው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲርል ራፋሞሳን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ሃራሬ ማእቀቡ ተነስቶላት ከገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ እንድትወጣ በሚጠይቁበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ከአሜሪካ በኩል  ማእቀቡን ለማራዘም በምክንያትነት የተጠቀሰው   ዚምባቡየ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ የሚፃረር ተግባር ከመፈፀም አልታቀብ ብላለች የሚል ነው፡፡

የአሜሪካ ባለ ስልጣናት የኤመርሰን ምናንጋግዋ መንግስት በሀገሪቱ የሚዲያ ነጻነት እንዳይኖር  እና ሰዎች ሀሳባቸውን በአደባባይ በተቃውሞ እንዳይገልፁ መከልከሉን ካልተወ ማእቀቡ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ምናንጋግዋ በበኩላቸው በፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የስልጣን ዘመን በወታደራዊ አዛዦች እና በመንግስት ተቋማት ላይ የተጣሉ ማእቀቦች እንዳሉ መቀጠላቸው ስህተት ነው በማለት እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡

አሜሪካ በዚምባቡየ በተለያዩ ግለሰቦች እና ንብረቶች ላይ 141 የሚሆኑ ማእቀቦችን መጣሏ ይታወሳል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *