loading

በእጅ የሚገፋ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የአፈርን አሲዳማነት የሚያክምና አፈርን የሚያዳብሩ ሁለት የምርምር ውጤቶች በሙከራ ላይ መሆናቸውንም ገልጿል ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር እንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ባለፉት አመታት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ ለሀገሪቱ መሰረት የሚሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

በግብርናዉ  ዘርፍ በእጅ የሚገፋ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ፤ የአፈርን አሲዳማነት የሚያክምና አፈርን የሚያዳብሩ ሁለት የምርምር ውጤቶች በሙከራ ላይ መሆናቸው፤ 20 ትውልድ ያለማቋረጥ ምርት የሚሰጠው የማሽላ ምርምር የምርት ማከማቸት ስራ ላይ መገባቱን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

በጤና ዘርፍ ለመድሃኒት ማጓጓዣነት የሚያገለግል ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ አብዝቶ ማምረት) ሊገባ መሆኑ፤ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህሙማን አስተዳደር ስርዓት ወደ ተቀናጀ ስርዓት ተቀይሮ ውጤታማ ስራ እየተሰራበት መሆኑ፤ የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩ የአንድ ዓመቱ ዉጤት ነብር ተብሏል፡፡

በማምረቻ ዘርፉ ደግሞ በኢትዮጵያ የተነደፈ በሚል በኢትዮጵያውያን የተነደፉ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ወደ ምርት እንዲገቡ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ስራዎች መጀመራቸው፤ ጋራዥ የሚሰሩ ባለሙያዎች የተለያዩ ማሽነሪዎችን እንዲያለሙ መደረጉ፤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞች ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ወደ ምርት እንዲገቡ መደረጋቸው ከመልካም ጅማሮዎች መካከል የተጠቀሱ ናቸዉ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *