loading
በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት:: ኮቪድ 19 በአፍሪካ መዛመቱን ቀጥሏል፤ በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 200 በላይ ከፍ ብሏልየሀገሪቱ መንግስት ይፋ ባወጣው መረጃ በደቡብ አፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች 1 ሺህ 280 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ደቡብ አፍሪካ ሁለኛውን ሞት ይፋ ያደረገች ሲሆን በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 31 የሚሆኑትን አክማ ማዳኗንም ተናግራለች፡፡የበሽታው ስርጭት በአፍሪካ አህጉር አሁንም እየጨመ መምጣቱን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ቫይረሱ የተከሰተ ሲሆን ኬንያ 42፣ ዩጋንዳ 33፣ ኢትዮጵያ 25፣ ጂቡቲ 18፣ ኤርትራ ደግሞ 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙባቸው ተረጋግጧል፡፡ግብፅ ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት በቫይረሱ ትልቅ ጉዳት የደረሰባት ሀገር ስትሆን በበሽታው ከተጠቁት 609 ሰዎች መካከል 40ዎቹ ህይዎታቸው ማለፉ ነው የተሰማው፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ 18 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት እና አንድ ሰው የሞተባት ማሊ ዜጎቿን ለምርጫ አደባባይ ማስወጣቷ ብዙዎቹን አስገርሟል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *