loading
በዘንድሮው ዓመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ::

በዘንድሮው ዓመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ዘንድሮ የሚተከሉ ችግኞች ያሉበትን ደረጃ በጎበኙበት ወቅት ነዉ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ሶደሬ አካባቢ በመገኘት ነው የችግኝ ማፍላት ስራውን ከክልሉ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር በመሆን የጎበኙት።በዘንድሮው አመት 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፥ ለዚህም የሚሆን ችግኝ የማዘጋጀት ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በ38 ሺህ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች እየተካሄደ እንደሚገኝ መግለፃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

አብዛኞቹ ችግኞችም ለምግብነት የሚውሉ እንደ አቦካዶእና ማንጎ ያሉ የፍራፍሬ ተክሎች ናቸው።የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታት ከተቻለ ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ችግኞቹን መትከል እንደሚጀመርም ገልጸዋል።ባለፈው አመት 4 ቢሊየን ችግኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ መተከሉን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የዝናቡ ሁኔታ ጥሩ ስለነበረ እና እንክብካቤ በመደረጉ ምክንያት አብዛኞቹ መጽደቅ መቻላቸውን እንደገለፁ ነው ዘገባው የጠቆመው።የዘንድሮውን ጨምሮ በቀጣይ 4 አመታት እስከ 20 ቢሊየን ችግኞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል እየተስራ መሆኑንም ጠቅላይሚንስትሩ ገልጸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *