የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ::
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ትምህርት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ:: የትምህርት የወደፊት ዕጣ ፈንታን የሚመለከተው ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ኮሚሽንን 2ኛ ስብሰባ ተካሂዷል።በዚህም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆኖነዋል።በውይይቱም የኮረሮ ቫይረስ በትምህርትና ልማት ላይ በረጅም ጊዜ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ለመከላከል የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማዘጋጀት መግባባት ላይ መደረሱን ከፕሬዚዳንት ፅሀፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።