loading
የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባን ጨምሮ 100 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ።

አርትስ 25/12/2010
የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት የተከሳሾቹን የክስ ሂደት እየተመለከተ ይገኛል።
ግለሰቦቹ በሃዋሳ ከተማና አካባቢዋ በሲዳማና በወላይታ ብሔረሰብ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ፥ ከ10 በላይ የሰው ህይወት እንዲጠፋና ዜጎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ ናቸው።
የፌደራል አቃቤ ህግም ክሱን በሁለት መዝገብ ያቀረበው ሲሆን፥ ጉዳያቸውም በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፌደራል ተዘዋዋሪ ችሎት እየታየ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል የሃዋሳ ከተማ ማረሚያ ቤት ኃላፊን ጨምሮ ስድስት የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ይገኙበታል።
ችሎቱም በማረሚያ ቤት ውስጥና በሃዋሳ ከተማ እና አካባቢዋ ለረጅም አመት በአብሮነት የኖሩትን የሲዳማና ወላይታ ብሄረሰብን በማጋጨት ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እየተመለከተ ይገኛል።
ኤፍ ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *