የግብጽ መገናኛ ብዙሀን ሟቹን ሴናተር ወቀሱ፡፡
በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአሜሪካው የምክር ቤት አባል ጆን ማኬይን በግብጽ የሙስሊም ብራዘርሁድ የሚባለው ተቋም የጡት አባት ነበሩ ብለዋቸዋል መገናኛ ብዙሀኑ፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በግብጽ የቴሌቭዥን ቶክ ሾው አቅራቢው አህመድ ሙሳ እርግጥ ነው ማኬይን ለአሜሪካውያን የጦር ጀግና ተደርጎ ይወደሳል ፤ እኛ ደግሞ የሙስሊም ብራዘርሁድ የተባለው አሸባሪ ቡድን መመሪያ አውጭና የመሪነት ሚና የነበረው ሰው መሆኑን እንመሰክራለን ብሏል፡፡
ሙሳ ለዚህ አባባሉ ማረጋገጫ አድርጎ ያቀረበው የሙስሊም ብራዘርሁድ ሰዎች በማኬይን የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለቀስተኛ ሆነው መታደማቸውን ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ማኬይን የነ ፕሬዝዳንት ኤርዶሀን እና የኳታሩ አሚር የቅርብ ወዳጅ ስለመሆናቸውና ከነ ትራምፕ የተለየ አቋም እንዳላቸው ለማሳየት ሞክሯል፡፡