loading
በ2011 በጀት ዓመት 53 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያላቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች ይጠናቀቃሉ ተባለ ፡፡

ከሚጠናቀቁት የመስኖ ፕሮጀክቶች ውስጥ 50 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው የዛሪማ ሜይ ዴይ ግድብ ግንባታ አንዱ ሲሆን በ15 ቢሊዮን ብር እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 2 የስኳር ፋብሪካዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
የዉሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ የኢትዮ- ናይል መስኖና ድሬይኔጅ ፕሮጄክት አካል የሆነው የርብ መስኖ መሬት ዝግጅት ፕሮጀክትም 3000 ሄክታር የማልማት አቅም አለው፡፡ አጠቃላይ ወጭውም 1.2 ቢሊዮን ብር ሲሆን ሲጠናቀቅ 6‚000 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡
በተጨማሪም የወይጦና አንገር ግድብ ዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ስራዎችም በበጀት ዓመቱ የሚጠናቀቁ ናቸው፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *