loading
አዲሱን ዓመት በደስታ እንድታከብሩ እሳትንና ኤሌክትሪክን በጥንቃቄ ተጠቀሙ ተብላችኋል፡፡

አርትስ 05/13/2010
በተቻለ መጠን ስራን ደራርቦ ባለመስራት ፤ተከፋፍሎ በመስራትና ስራን ሳይመሽ በግዜ በማጠናቀቅ አደጋን መከላከል ይቻላል ብሎናል የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የአዲስ አመት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያከብረዉ በዓል መሆኑና በሁሉም ቤት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ፍጆታና እሳትን መጠቀም ስለሚኖር አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከጥንቃቄም አልፎ አደጋ ካጋጠመ ለበአሉ በሁሉም ቅርንጫፎች በተለየ መልኩ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ተናግሯል፡፡
አደጋ ሲያጋጥምም ወዲያዉ በነጻ የስልክ ቁጥራችን 939 ወይም 0111555300 በመደወል አሳውቁን ተብላችኋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *