loading
የፌደራል ፖሊስ የፊታችን ቅዳሜ ወደ አገር ቤት የሚገቡ የኦነግ አመራሮች አቀባበል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት አድርጌአለሁ አለ፡፡

አርትስ 03/01/2010
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል አቶ ዘይኑ ጀማል ለኢቢሲ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት በአንዳንድ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የኦነግን አርማ በሚሰቅሉና በአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል ግጭቶች ተከስተዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች አርማቸውን ይዘው የሚመጡ ወጣቶችን የመከልከልም ሆነ የመፍቀድ ሀላፊነት የፖሊስ በመሆኑ አርማ የሚሰቅሉ ወጣቶችን መከልከል የለባቸውም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የኦነግን አርማ በየአካባቢው የሚሰቅሉ ወጣቶችም የህዝብ መገልገያ የሆኑ አውራ ጎዳናዎችንና ፖሎችን ቀለም ከመቀባት መቆጠብ አለባቸው ብለዋል።
መኪና የመስበርና ድንጋይ የመወርወር፣ ተቀጣጣይ ጋዝ ይዞ ፖሊስ ጣቢያዎችን ለማቃጠል የመሞከር አዝማሚያዎች እየታዩ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ፤ማንም ሰው ጉልበተኛ ነኝ ብሎ በህዝብ ላይ፣ በአገር ተቋማት ላይ ጉዳት ሲያደርስ ፖሊስ ህግን የማስከበር ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
አርማ ይዞ መውጣት ፖሊስ አልከለከለም፣ ማንማ ሰው የራሱን አርማ ይዞ በሰላማዊ መንገድ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ምንም ጉዳት እንደሌለውም አቶ ዘይኑ ጀማል አስታውቀዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *