loading
ሩሲያና ቻይና ግዙፉን የጦር ልምምድ ጀምረዋል 

አርትስ 03/02/2011
ሩሲያና ቻይና ኢስት 2018 የተሰኘውን ወታደራዊ ልምምዳቸውን በሩሲያና ቻይና ድንበር አቅራቢያ ጀምረዋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትእይንቱን ለመከታተል በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በጦር ልምምዱ ላይ ከሁለቱ ሀገራት የተውጣቱ 300 እንዲሁም 36 ሺህ ታንኮች ሺህ ወታደሮች ይሳተፉበታል፡፡
ፑቲን ሲናገሩ ወታደሮች ሁልጊዜም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ዝግጁ መሆን ስላለባቸው ፤ የአሁኑ ልምምም የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ውጭ ለሚያስቡት ግን ሩሲያ ምንጊዜም ሰላም ፈላጊና ከየትኛውም ሀገር በአጋርነት ለመስራት በሯ ክፍት ነው በማለትም ልምምዱ ማንንም ለመስፈራራት አለመሆኑን አብራርተዋል፡፡
ቻይና እና ሩሲያ የሚያካሂዱት ወታደራዊ ልምምድ የቀድሞዋ ሶቬት ህብረት ከተበታተነች በኋላ በትልቅነቱ የሚጠቀስ ነው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *