የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ አየር ኃይል ስኳድሮን በአሸባሪው አልሻባብ ሰራዊት ላይ ድልን ተቀዳጀ፡፡
አርትስ 05/01/2011
ሰሞኑን አልሻባብ በአሚሶም ጥላ ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሰራዊት ለማጥቃት ሞክሮ እንደነበር የተነገረ ሲሆን ሰራዊቱ ለመቀያየር በጎዞ ላይ እንደነበር ተነግሯል፡፡
ይህንን ተከትሎ ታዲያ አየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በአልሻባብ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ከ70 በላይ የአልሻባብ አባላትና ከባድ መሳሪያ የጫኑ ሁለት ተሸከርካሪዎች አየር ኃይሉ ማውደሙም ተነግሮዋል፡፡
ብርጋዴር ጀነራሉ ከስምሪት በፊት ቡድኑን ለማጥቃት ከፍተኛ ጥናት መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
ጥናቱንም ተከትሎ በወሰደው እርምጃ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ግቡን መምታቱንም አንስተዋል፡፡
ብርጋዴር ጄነራሉ የምድርና የአየር ኃይሉ ጥምረት አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅሰው ይህ ጥምረትም ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በሌሎች አካባቢዎች ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ያለብዙ ኪሳራና ወጪ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መመከት ይገባል ብለዋል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ