loading
የተለያዩ አገራት የኢህአዴግ አቻ ድርጅት ተወካዮች የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አርትስ 23/01/2011
በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የተገኙት ዘጠኙ የውጭ አገራት ፓርቲዎች ተወካዮች ፓርኩን ከጎበኙ በኋላ አድናቆታቸውን በመግለፅ በየአገራቸው ስላለው የኢንደስትሪ ሂደት በመግለፅ ከኢትዮጵያ በተለይም ከሃዋሳ የተለየ ልምድ ማግኘታቸውን ለአርትስ ተናግረዋል።
ጉብኝቱን ያስተባበሩት የኢህአዴግ ፅ/ቤት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሰጠኝ ድርጅቱ ጉባዔውን ሲያካሂድ መክፈቻው ላይ የተገኙ አቻ ድርጅቶች በአገሪቱ ያለውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲገነዘቡ ፓርኩን እንዲጎበኙ ተደርጓል ብለዋል።
የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የውጭ ባለሀብቶች በአምራቹ ዘርፍ እንዲሰማሩ ዕድል የፈጠረ ሲሆን በሶስት መቶ ሄክታር መሬት ላይ አርፏል። ፓርኩ እስከ መቶ ሺህ ለሚደርሱ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *