loading
ከከባዱ ርእደ መሬት በኋላ በኢንዶኔዥያ ህይወት ቀጥላለች፡፡

በፈረንጆቹ መስከረም 28 በኢንዶኔዥያ በተከሰተው ርእደ መሬት ከ 1 ሺህ 900 በላይ ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡
ርእደ መሬትንና የጭቃ መንሸራተትን በአንድ ጊዜ ያስተናገደችው የፓሉ ከተማ በርካታ ነዋሪዎቿ አሁንም ድረስ የገቡበት አልታወቀም፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው በዚህች ከተማ እና አቅራቢያዋ ከ5 ሺህ በላይ ዜጎች በመሬት መንሸራተት ሳቢያ ሳይሰወሩ እንዳልቀሩ ተዘግቧል፡፡
አሁን ከአስር ቀናት በኋላ ህፃናቱ እየተንጠባጠቡም ቢሆን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ መጀመራቸውን መምህራን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ትምህርት ቤታቸው ፈራርሶ በማየታቸው ያዘኑ ሲሆን የትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎችም ህፃናቱ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ አናስገድዳቸውም ፤ ምክንያቱም ገና ከጭንቀታቸው አላገገሙም ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *