loading
ሂልተን ሆቴል ሊሸጥ ነው::

አርትስ 02/02/2011
መንግስት በሆቴል ዘርፍ ላይ የነበረውን ተሳትፎ ለማስቀረት የደረሰበትን ውሳኔ ተከትሎ ነዉ ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ መንግስት በይዞታው ስር ያስተዳድረው የነበረውን ሂልተን ሆቴል ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ ያለዉ።
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት መንግስት ሆቴሉን በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ በያዝነው ዓመት ፍላጎት ላላቸው የሃገር ውስጥም ይሁን አለም አቀፍ አካላት በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።
ላለፉት በርካታ አመታት ሆቴሉን ከመንግስት በኮንትራት ተረክቦ እያስተዳደረ የሚገኘው ሂልተን ኢንተርናሽናል የተባለው የውጭ ሃገር ኩባንያ ሲሆን ሆቴሉን ጠቅልሎ የመግዛት አቅም ካለው በጨረታው ከመሳተፍ የሚያግደው ነገር እንደሌለም አቶ ወንዳፍራሽ ጠቁመዋል።
ጨረታው መቼ እንደሚወጣ ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ሆቴሎች በሙሉ በስፋት ቀዳሚው መሆኑ የሚነገርለት ሂልተን ሆቴል ስድስት መቶ መኪኖች የሚያስቆም ስፍራ ያለው ሲሆን አለምአቀፍ ደረጃውን ያሟላ መዋኛ እና አራት የቴኒስ መጫወቻ ሜዳ እንዲሁም አምስት ትልልቅ የስብሰባ አዳራሾችን ያካተተ ግዙፍ ሆቴል ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *