loading
ፈረንሳይ ለአዲስ አበባ የፅዳት ልምድ ልታካፍል ነው

አርትስ 03/02/2011

 ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የፈረንሳዩን አምባሳደር ፍሬድሪክ ቦንተምስን በፅ/ቤታቸዉ ሲያነጋግሩ የከተማዋ ቆሻሻ አንዱ ርዕሰ ጉዳያቸው ነበር ።                                                                 በውይይታቸውም በከተማዋ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣በአረንጓዴ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።አምባሳደር ፍሬድሪክ የፈረንሳይ ከተሞች በፅዳት እና በስነ ህንፃ ውበት ዙሪያ ያላቸውን መልካም ተሞክሮ ለአዲስ አበባ ለማካፈል እና በሰው ሀይል ስልጠና ላይ ለመዲናዋ ድጋፍ ለማድረግ ፈረንሳይ ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *