loading
የቱርክ ፖሊስ የጀማል ካሾጊን አስክሬን ጫካ ዉስጥ እየፈለገ ነው

“ጋዜጠኛ ጃማል ካሾጊ በሳዉዲ ተገድሏል አስከሬኑም በአቅራቢያ በሚገኝ ጫካ  አልያም በእርሻ ማሳ ዉስጥ ሳይጣል አልቀረም” የሚለው የቱርክ ፖሊስ የሟቹን አስከሬን ፍለጋ መጀመሩን አስታውቋል።

ቢቢሲ እንደዘገበው ሳዑዲ አረቢያ ጋዜጠኛዉን ምን አጋጥሞት እንደተሰወረ የማዉቀዉ ነገር የለኝም በማለት ማስተባበሏን ቀጥላለች፡፡

በሌላ በኩል አንድ የቱርክ ከፍተኛ ባለስልጣን ለኤቢሲ ኒውስ የሰጡትን መግለጫ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው ረቡዕ ዕለት ወደ ቱርክ ያቀኑት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ የጋዜጠኛዉን ግድያ የሚያስረዳ የድምጽ ማስረጃ ከሰሙ በኋላ ቆየት ብለዉ መስማታቸዉን አስተባብለዋል ፡፡

የጋዜጠኛዉ ጉዳይ ሪያድንና ምዕራባዉያን ወዳጆቿን ዉዝግብ ዉስጥ ያስገባ በመሆኑ በቀጣይ ሳምንት በሪያድ በሚካሄደዉ ኢንቨስትመንት ኮንፍረንስ ላይ የአሜሪካዉ ግምጃ ቤት ሃላፊ ስቲቨን ምኑቺን እና የእንግሊዝ  አለምአቀፍ ንግድ ሃላፊዉ ሊያም ፎክስ በጉባኤዉ ላይ ላይሳተፉ እንደሚችሉ እየተዘገበ ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *