የጃማይካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በቦብ ማርሌ ሴት ልጅ ድጋፍ ታግዞ ወደ አለም ዋንጫው ማለፍ ቻለ
አርትስ ስፖርት09/02/2011
ቦብ በጃማይካ እውቅና እና ተወዳጅ የሙዚቃ ሰው ሲሆን የአብራኩ ክፋይ የሆነችው ደግሞ በስፖርቱ ዘርፍ እያደረገች ባለችው ተሳትፎ እና ስኬት ስሟ እየተወደሰ ይገኛል፡፡
ለዚህ ውዳሴ መነሻው ደግሞ የጃማይካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከስምንት አመታት በፊት ለቡድኑ የሚያደርገውን የገንዘብ እገዛ አቋረጠው፡፡
ነገር ግን እ.አ.አ በ2014 ሴዴላ ማርሌ የብሄራዊ ቡድኑ ይፋዊ አምባሳደር በመሆን መሾሟን እና መስራት መጀመሯን ተከትሎ እንዲሁም የአላከራን ፋውንዴሽን አጋዥነት በቅፅል ስሙ የሬጌ ገርልዝ እየተባለ የሚጠራው ቡድን የአለም ዋንጫውን ዘመቻ ጀመረ፡፡
በዚህም በሚቀጥለው አመት በፈረንሳይ ደጋሽነት ለሚካሄደው የእንስቶች አለም ዋንጫ ለመሳተፍ በኮንካካፍ ዞን፤ ጃማይካውያን የፓናማ አቻቸውን በመርታት ከካሪቢያን ሀገራት ለአለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ በማለፍ ህልማቸውን፤ ምስጋና ለሴዴላ ማርሌ ቸርነት ይግባና ማሳካት ችለዋል፡፡
ሴዴላ በ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክ ውድድር የጃማይካ ቡድን የመወዳደሪያ ትጥቅ ዲዛይን ያደረግችው እርሷ ነበረች፡፡