loading
በመጭው እሁድ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የአምስተርዳም እና የኒው ደልሂ የማራቶን ውድሮች ይካሄዳሉ

አርትስ ስፖርት 09/02/2011
የአምስተርዳም ማራቶን እ.አ.አ ከ1975 ጀምሮ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በIAAF የወርቅ ደረጃ የተሰጠው ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ43ኛ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ በውድድሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወንድና ሴት አትሌቶች ይካፈላሉ እነዚህም፡-
በወንዶች፤ ቀነኒሣ በቀለ፣ የኔው አላምረው፣ ሙሌ ዋሲሁን፣ ሰለሞን ድንቄሳ፣ ታዱ አባተ እና ጎሣ ቦጋለ ሲሆኑ በሴቶች ደግሞ መሠረት ደፋርን ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን መድረክ እንመለከታታለን፤ በተጨማሪም መሠረት በለጠ፣ ታደለች በቀለ፣ መሠረት ጎላ፣ ዝናሽ መኮንን፣ አዝመራ ገብሩ እና ሻሾ አለሙ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
በህንድ ኒው ደልሂ ግማሽ ማራቶንም በርካታ ኢትዮጵያውያን ተካፋይ የሚሆኑ ሲሆን በሴቶች አትሌት ጥሩነሽ ዲባባን ጨምሮ፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ አባበል የሻነው፣ ወርቅነሽ ደገፋ፣ ዘይነባ ይመር እና ፀሀይ ገመቹ ይሰለፋሉ፡፡
በወንዶች ፈይሳ ለሊሳ፣ ሃጎስ ገ/ህይወት፣ አንዱአምላክ በልሁ፣ ጌታነህ ሞላ፣ ልኡል ገ/ስላሴ እንዲሁም በተስፋ ጌታሁን ይካፈላሉ፡፡
ውድድሩ ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን በIAAF የወርቅ ደረጃ ተሰጥቶት ከ2005 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በውድድሮቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከተቀናቃኞቻቸው ጠንከር ያለ ፉክክር ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
አርትስ ለአትሌቶቹ መልካም ውጤትን ይመኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *