loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ21ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከሱዳን ጋር ተፈራረመ

ሽንዋ እንደዘገበዉ የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት በሰሜን ሱዳን ዋይት ናይል ግዛት መጠለያ ዉስጥ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ለመደገፍ 21 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ከሱዳን ጋር ተፈራርሟል፡፡

ትናንት በተደረገዉ ስምምነትም ለስደተኞቹ የሚደረገዉ ድጋፍ 3 ደረጃዎች ያሉት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፉም ለግብርና መገልገያ መሳሪያዎች የሚውል  ሲሆን  ከ2.2 ሚሊዮን ዶላር  በላይ ተይዞለታል ተብሏል፡፡

ድርጅቱ የሚያደርገዉ ድጋፍ ስደተኛዉ በግብርና ዘርፉ ላይ ተሰማርቶ ዉጤታማ እንዲሆን የሚያግዝና በስፍራዉ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተደራሽ እንዲሆን የሚያስችል ነዉ ሲሉ የዋይት ናይል ግዛት  የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነሩ ሃማድ አል ጂዙሊ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እነደገለጹት በሰሜን ሱዳን ዋይት ናይል ግዛት ከ150 ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳን ስደተኞች በመጠለያ ጣቢያ ዉስጥ የሚኖሩ ሲሆን 88ሺህ ያህሉ ደግሞ በተለያዩ ከተማዎች ይኖራሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *