loading
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አፍሪካን ይጎበኛሉ

አርትስ 13/02/2011

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ቲቦር ፒ ናጊ  አፍሪካን ይጎበኛሉ

ሃላፊው በቅርቡ በአፍሪካ ስለሚያደርጉት ጉብኝትና አሜሪካ በአፍሪካ ላይ በምትከተለው ፖሊሲ ዙሪያ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከጋዜጠኞች ጋ የስልክ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍርካ ጉዳዮች ቢሮ በአህጉሪቱ ልማት እና አሜሪካ በአፍሪካ በምትከለተው ፖሊሲ አስተዳደር ላይ አትኩሮ ይሰራል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ለአርትስ ቲቪ ከላከው መግለጫ መረዳት እንደተቻለው ቢሮው  በተጨማሪም የዴሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር፣ የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት በመደገፍ እና ሰላምና ጸጥታን በማስፈን እንዲሁም ልማትና እድገትን በማፋጠን በሚሉ አራት አበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *