loading
ኢሉድ ኪፕቾጊ የተመድ የዓመቱ ሰው ተብሎ ተመረጠ

አርትስ 15/02/2011

 ኬንያዊው የዓለም ማራቶን ሪከርድ ባለቤት ኢሉድ ኪፕቾጊን የአመቱ ሰው ብሎ የመረጠው  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅት ነው፡፡

ተመድ ለኪፕቾጊ የዓመቱ ሰው በማለት ዕውቅና ያበረከተው በኬንያ ከኤችአይቪ ጋር በተያያዘ  በሰራው በጎ ተግባር  ሲሆን የዕውቅና ስነስርዓቱኬንያ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት ተከናውኗል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የተገኘው ኪፕቾጊ ስለዕውቅናው ያመሰገነ ሲሆን በበጎ ምግባሩ እንደሚቀጥልበትም ቃል ገብቷል፡፡

የ33 ዓመቱ ኪፕቾጊ ከአንድ ወር በፊት በርሊን በተካሄደው አለም አቀፍ የማራቶን ውድድር  ሪከርድ መስበሩ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *