የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃለ ፈፀሙ
አርትስ 15/02/2011
የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 2ኛ ልዩ ስብሰባ የዶክተር ሙላቱን መልቀቂያ ተቀብሎ
በምትካቸው አምባሳደር ሣህለ ወርቅ ዘውዴን ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል፡፡
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃለ በፈፀሙበት ወቅት የጀመርነው የለውጥ ጉዞ በሴቶች እና በወንዶች እኩል ተጠቃሚነት ከተመራ በእኩል የምንኖርባት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን ፤ እርስ በርስ በመፈቃቀር እና በመከባበር አድነታችንን በሚያጠነክሩ ጉዳች ላይ መጠንከር ይገባናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በዳበረ በቤተ እምነታችን እና በሽምግልና ጥበባችን ችግሮቻችንን መፍታት ይጠበቅብናል በማለት በአፍሪካ ባልተለመደ መልኩ ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳን ዶክተር ሙላቱን አክብረው ለዚህ ስልጣን የመረጣቸውን ህዝብ አመስግነዋል፡፡