loading
ሱዳን የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ ቀንድ ኩራት ነው አለች

አርትስ 15/02/2011

ኢትዮጵያ፤ ግብፅና ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በጋራ ስምምነት ላይ ተመርኩዞ ሊካሄድ እንደሚገባ መስማማታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር እንደተናገሩት ስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ኩራት ነው።

ግድቡ ከአፍሪካ አህጉር ትልቁ የሃይል ማመንጫ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአባይ ተፋሰስ ሃገራት የሆኑት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ እነዚህን በጎ ተስፋዎች ወደ ስራ ቀይረው የግንባታ ሂደቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ከስምምነት መድረሳቸው ግድ ሊሆን ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ።

የአባይ ወንዝ ለሶስቱም የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት የኢኮኖሚ ዋልታ ቢሆንም ግብፅ ለዘመናት ሲጠቅመኝ የነበረውን ወንዝ ማጣትም ሆነ በመጠን እንዲቀንስብኝ አልፈልግም ባይ ናት፡፡

ኢትዮጵያ የግድቡ ግንባታ ግብፅን በምንም መልኩ እንደማይጎዳት በተደጋጋሚ መናገሯ ይታወሳል ብሏል ሮይተርስ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *