loading
ኦስማን ሳሌህ የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት ያለማንም ጣልቃገብነት የተካሄደ ነው አሉ

ኦስማን ሳሌህ የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት ያለማንም ጣልቃገብነት የተካሄደ ነው አሉ

አርትስ 16/02/2011

ኤርትራና ኢትዮጵያን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በጋራ መስራታቸዉን ቀጥለዋል አሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ ፡፡

አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው የሰኔ ስምንቱ የሰላም ስምምነት የለማንም ጣልቃ ገብነት በሁለቱ ሃገራት በጎ ፍቃድ ላይ ተመስርቶ የተካሄደ ነው፡፡

የዉጭጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መታደስ ብዙዎች እንደሚያስቡት በብዙ ጫናና በሌላ አካል ግፊት የተደረገ አይደለም።

የስምምነት ሂደቱ የተጀመረው የኤርትራ ልኡክ አዲስ አበባ በገባበት ቅፅበት ጀምሮ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ወቅቱም የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች በአካል ብቻ የተገናኙበት ሳይሆን በሃሳብም ልብ ለልብ የተወያዩበትና የተስማሙበትም ጭምር እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ኦስማን እንዳሉት ኢትዮጲያና ኤርትራ ዕርቅ ፈፅመው ብቻ ቁጭ አላሉም፤ ያለፉትን የባከኑ  ጊዜያት የሚተኩ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ቅድሚያ የሚሰጡት ለጋራ ፕሮጀክትና ኢንቨስትመንት ነው ብለዋል ፡፡

የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ፤  በኤርትራና ሱማሊያ መሃከል ዘላቂ ሰላም ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታና በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ማስነሳት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ  ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *