loading
ሁለት የእንግሊዝ ሚኒስትሮች ሃገሪቱ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ባላት ግንኙነት ዙሪያ ምርመራ ሊጣራባቸው ነው

አርትስ 19/02/2011

በእንግሊዝ የመካከለኛው ምስራቅ ሚኒስትር አሊስታየር በርት እና የውጭ ጉዳይ ጸሃፊው ጀረሚ ኸንት እንግሊዝ ከሳዑዲ አረቢያ ጋ ባላት ጠቅላላ ግንኙነት ዙሪያ ለየብቻ ይመረመራሉ ብሏል የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት።

የእንግሊዝ ጋዜጦች እንደሚሉት ግን ሳዑዲ አረቢያ ጋዜጠኛ ካሾጊን በቁጥጥር ስር ለማዋል አለያም ለመግደል እያሴረች እንደነበር የእንግሊዝ የደህንነት መዋቅር አስቀድሞ ያውቅ ነበር።

ይህንን ተከትሎም ሁለቱ ሚኒስትሮች እንግሊዝ ለሳዑዲ መሩ የየመን ጦርነት ስለምታደርገው ድጋፍ እንዲያብራሩ በዚህ ሳምንት ጫና በርትቶባቸው ነበር የከረሙት።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ግን በሁለቱ ሚኒስትሮች ላይ የሚካሄደው ምርመራ ከጀማል ካሾጊ ግድያም ይሁን ሳዑዲና የመን ከገቡበት ጦርነት ጋር የሚያያይዘው ምንም ነገር የለም ነው የሚለው።

እንግሊዝ እንደምታምነው  በኢራን የሚደገፉት የሃውቲ አማጺያን በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈውን የየመን መንግስት ማጥቃት መጀመራቸው በሳዑዲ አረቢያ ላይ ግልጽ የሆነ ስጋት ደቅኖባታል።

 

ስለሆነም ሳዑዲ በየመን ላይ ላለፉት አራት አመታት ስታካሂድ የቆየችው ጦርነት የአለምአቀፉን ሰብዓዊ መብት ህግ የሚጥስ ባለመሆኑ እንግሊዝ ለሃገሪቱ የጦር መሳሪያ መሸጥ ልክ እንደሆነ አቋም ይዛለች።ዘገባው የ ዘጋርዲያን ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *