loading
ሱዳን ሩስያ በቀይባህር ዳርቻ ወታደራዊ ቀጠና እንድትገነባ ፈቀደች

ሱዳን ሩስያ በቀይባህር ዳርቻ ወታደራዊ ቀጠና እንድትገነባ ፈቀደች

አርትስ 20/02/2018

ሁለቱ ሃገራት በወታደራዊ  ጉዳዮች  ላይ በጋራ ለመስራት መወያየታቸውም ተነግሯል።

ውይይቱን ያደረጉት የሱዳን መከላከያ ዋና አዛዥ ከማል አብደል ማሩፍ እና የሩሲያ መከላከያ ምክትል አዛዥ ናቸው፡፡

የውይይቱን ውጤት ተከትሎ ፕሬዚዳንት አልበሽር ሩስያ በቀይ ባሕር ዳርቻ ወታደራዊ ቀጠና እንድትገነባ  ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል።

በተጨማሪም የሱዳንን ወታደሮች በሩሲያ ሰራሽ የጦር መሳሪያዎች ለማስታጠቅ  ከስምምነት  ላይ ደርሰዋል፡፡

ፕሬዚዳንት አልበሽር  ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሜር ፑቲን ጋር ተገናኝተው የመከሩት የ2018 የዓለም ዋንጫን ለመከታተል ሞስኮ  በሄዱበት ወቅት  ነው።

ሁለቱ መሪዎች በወታደራዊ ትብብር ለመጣመር መስማማታቸውን ተንተርሶ ነው የጦር አዛዦቻቸው ወታደራዊ ስምምነት ላይ የደረሱት ።

ሱዳን ከወታደራዊ ትብብሩ በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማጠናከር  እንደምትፈልግም ተነግሯል፡፡ ዘገባው የሱዳን ትሪቢዩን ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *