loading
ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ የክብር እንግዳ ነው

አርትስ ስፖርት 23/02/2011

18ተኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ህዳር 9/2011 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ በዚህ ሁነት ላይ የበርካታኢትዮጵያውያን እና ኬንያዊያን የመካከለኛና ረዥም ርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች ተቀናቃኝ የሆነው ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ በክብር እንግድነትይታደማል እየተባለ ይገኛል፡፡ አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ በተለይ በአስር እና አምስት ሺ ሜትር ርቀቶች አሁን ደግሞ በማራቶን ከሚወዳደሩት አትሌቶችይጠቀሳል፡፡ በዚህ አመታዊ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሁነት/ ውድድር ከ40,000 በላይ ተሳታፊዎች ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ በርካታ ስመጥር እናወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ጨምሮ ከጎረቤት የአፍሪካ አህጉር እና ሌሎች አለማት ሀገራት አትሌቶች እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች ይካፈላሉተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *