loading
በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ያለውን የገቢና ወጪ ንግድ ለመቆጣጠር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው

አርትስ 24/02/2011

ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ነዳጅን ጨምሮ በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ ገደብ እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

በአገሮቹ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በሁለቱ መንግስታት በተደረሰ የሰላም ስምምነት መሰረት ድንበሮች ተከፍተው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጀምሯል።

በሁለቱ አገሮች መካከል የሚደረጉ የገቢና ወጪ ዕቃዎችን ለመቆጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ማዕቀፍ እያዘጋጀ ነው።

ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትንም ሆነ ወደ ኤርትራ የሚላኩትን ዕቃዎች ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ እየተረቀቀ ነው።

በዚህም ወደ አገር የሚገቡትም ሆነ ወደ ኤርትራ የሚላኩ ዕቃዎች ከሌሎች አገሮች ጋር እንደሚደረገው የንግድ ልውውጥ የቀረጥ ስርዓት ይዘረጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የንግድ ልውውጥ ስምምነት በመንግስታት ደረጃ ለማድረግ የሚያግዝ መረጃም በሁለቱ አገሮች ድንበር አካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከፌደራልና ከትግራይ ክልል መንግስት ተቋማት በተውጣጡሙያተኞች መረጃ መሰብሰቡም ታውቋል።

የባለሙያዎቹን መረጃ መሰረት በማድረግ የድንበር ግንኙነት በአሁኑ ወቅት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ክፍት እንዲሆን ተደርጓል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *