loading
የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በፈረንጆቹ 2018 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.5 ከመቶ ያድጋል አለ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በፈረንጆቹ 2018 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.5 ከመቶ ያድጋል አለ

አርትስ 28/02/2011


አይ ኤም ኤፍ ይህንን ያለዉ ኢትዮጵያ ከአለም ገንዘብ ድርጅት ጋር ብድርን በተመለከተ በተወያየበት ወቅት መሆኑን የፋይናንስ ሚኒስቴር ገልጸል፡፡

 

በውይይቱ የዓለም የገንዘብ ድርጅት የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት እንዲሁም የብድር ሁኔታ ገምጋሚ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሁኔታ አድንቀዋል ተብሏል፡፡

የፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ባለፉት 20 ዓመታት የኢትዮጵያ የሐገር ውስጥ ምርት (GDP) 10 እጥፍ ያህል ማደጉን ተናግረዋል፡፡

የነፍስ ወከፍ ገቢም እ.ኤ.አ በ1999 ከነበረው 128.8 ዶላር በአሁኑ ወቅት ወደ 872.8 ዶላር ከፍ ማለቱን ገልፀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *