loading
በከተማ ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መጠን ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

በከተማ ያለው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት መጠን ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ

አርትስ 29/02/2011

 

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው በአለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት በአንድ ሀገር ያለው የኤች አይ ቪ ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ ያ ሀገርበበሽታው ወረርሽኝ ገብቷል።

በኢትዮጵያ ያለው የበሽታው ስርጭት ሲታይ ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም በከተማ ደረጃ ያለው ስርጭት ግን ወረርሽኝ ደረጃ ደርሷል ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሻሎ ዳባ እንዳሉት በከተማ ያለው የበሽታው የስርጭት መጠን ከገጠሩ በ7 እጥፍ መብለጡን ያሳያል ።

በከተማ ብቻ የሚኖሩ 23 ሺህ ያህል ሰዎችን ናሙና በመውሰድ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው በሴቶችላይ  ያለው የበሽታው ስርጭት መጠን 3 ነጥብ 6 በመቶ ሆኗል።

በወንዶች ላይ ያለው የስርጭት መጠን ደግሞ 1 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል ብሏል ጥናቱ።

ከሁለት አመት በኋላ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ እንዲሁም የሚሞቱትን ሰዎች ቁጥር 75 በመቶ ለመቀነስ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል። ዜናው የፋና ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *