loading
ፖሊስ ምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት እየሰራሁ መሆኑን ገለጸ

አርትስ 29/02/2011

 

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጅዓለም እንደተናገሩት በዞኑ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግርለመፍታት የክልሉ ፖሊስና የፌደራል የፀጥታ አካላት በቅንጅት እየሰሩ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም አካባቢውን ወደ ነበረበት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ከአካባቢው ማሕበረሰብ፣ ከመንግስትአመራሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከወጣቶች ጋር በመተባባር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር በተገበረው የተቀናጀ ስራ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ወደ ነበረበት አንፃራዊ ሰላም መመለሱንኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ተሳትፈው የነበሩና  በዘረፋና በተለያዩ ወንጀሎች ተሰማርተው የነበሩ  ተጠርጣሪዎችምበቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ተብሏል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *