loading
በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክ አመራርና ሰራተኞችን በተመለከተ የፌደራል ዓቃቤህግ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል

አርትስ 03/03/2011

 

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ 40 የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ አመራርና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት እንደቀጠለም ተሰምቷል፡፡ የስራ ሃላፊዎቹና ሰራተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት በይፋ አልተነገረም፡፡ ዛሬ የፌደራሉ  አቃቢ ህግ በቅርቡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ እና በቁጥጥር ስር እየዋሉ በሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች እና በሌሎች ወቅታዊ የፍትህ ጉዳዮች  በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *