loading
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሳን ሱኪን ሽልማት ነጠቃቸው

አርትስ 04/04/2011

የማይናማሯ መሪ አውንግ ሳንሱኪ በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ሲፈፀም ዝምታን መምረጣቸው ነው በፈረንጆቹ 2009 የሞራል አምባሳደር ተብለው የተሰጣቸውን ሽልማት ያስነጠቃቸው፡፡

 

ሮይተርስ እንደዘገበው በተባበሩት መንግስታት ስልጣን የተሰጠው የምርመራ ቡድን በማይናማር የተፈፀመው የዘር ማጥፋት፣ የአስገድዶ መድፈርና ሰዎች እንዲገደሉ ቅስቀሳ የማካሄድ ወንጀል መሪዋ ተጠያቂ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

 

ይሁንና የማይናማር መንግስት የምመራ ውጤቱን ወደ አንድ ወገን ያደላና ሚዛናዊነት የጎደለው በማለት አልተቀበለውም፡፡

 

መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገው አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሳን ሱኪ የሀገራቸው ጦር ሀይል በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም እያዩ ዝም ማለታቸው አሳፋሪ ነው በማለት ተችቷቸዋል፡፡

 

ከ700 ሺህ በላይ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች የማይናማር ወታደሮችን ጥቃት ሸሽተው በጎረቤት ባንግላዲሽ ተጠልለው ይገኛሉ፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *