loading
የፌዴራል መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አደነቀ።

አርትስ 5/03/2011

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫው፥ የኢፌዴሪ መንግስት በሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ እና በሀገሪቱ ላይ ከባድ የሙስና የወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ የበላይነት አንዲከበር እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ ነው ብሏል።
የክልሉ መንግስት፤ የኢፌዴሪ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያደንቃል ብለዋል፤ የሚጠበቅበትን ድጋፍ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
በህግ በምትተዳደር ሀገር ውስጥ በሰው ልጅ ላይ ለመፈፀም ይቅርና ለማሰብ የሚከድብ ተግባር በመፈፀም እንዲሁም የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል ከሀገር ክህደት ተለይቶ እንደማይታይም መግለጫው አትቷል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ ማንኛውም ሰው ከህግ ማምለጥ አንደማይችል እና ከሀገሪቱ ህገ መንግስት በላይ እንዳልሆነ እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑንም ገልጿል።
ተግባሩ  ለህግ የበላይነት መከበር በቁርጠኝነት እንዲሰራ የሚያነሳሳ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል።
ሌባ መቼም ቢሆን ከህዝብ አይን እና ጆሮ ማምለጥ አይችለም ያለው መግለጫው፥ የክልሉ ህዝብም በማንኛውም ህገ ወጥ ተግባርን መከላከል ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *