በኢትዮጵያ የስኳር ህመም ስርጭት አስጊ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
አርትስ 05/03/2011
በኢትዮጵያ ካለው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር 3 በመቶ የሚሆነው የስኳር በሽታ ታማሚ እንደሆነ የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር አሳወቀ፡፡
አገር አቀፍ የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ዳሰሳ ጥናት በተሳካ ሁኔታ የተከናወነ መሆኑን ያሳወቀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለቁጥጥርና ክትትል ስራዎች እገዛ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር አብዱራዛቅ አህመድ በበኩላቸው መሰራት ያለባቸው ስራዎች ካልተሰሩ ቁጥሩ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል አሳውቀዋል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ነገ በዓለም አቀፍም በኢትዮጵያም ደረጃ ለ28ኛ ጊዜ ዛሬ በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡
ቀኑ በብሔራዊ ትያትር ‘የስኳር ህመም ይመለከተኛል” በሚል መሪ ቃል የስኳር ህመምን ለመከላከል ቤተሰብ ባለው ሚና ላይ ተመስርቶ ይከበራል።