loading
የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት አለኝ አለች

አርትስ 05/03/2011

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢ.ፌ.ዲ..ሪ አምባሳደር ተበጀ በርሄ ከአገሪቱ የበጎ አድራጎት ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ሰኢድ አበዱልጋህኒ ጋር ተወያይተዋል።

የድርጅቱ ምክትል ዳይሬክተር ድርጅታቸው በአገራችን በተለያዩ ክፍሎች የሰብአዊ እርዳታ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት በባሌ ዞን ሮቤከተማ ት/ቤቶችና ሆስፒታሎችን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስረድተው፤ በተለያዩ የሀገራችን ክልሎች የቦጎ አድራጎት ስራዎችን ለማከናወን ዕቅድእንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀበይ ፀህፈት ቤት እንደገለፀው አምባሳደር ተበጀ በበኩላቸው ድርጅቱ እስከሁን በኢትዮጵያ ያከናወናቸውን በጎ ተግባራት አድንቀው በጅምር ላይያሉ የልማት ስራዎች እንዲጠናቀቁም ኤምባሲው የሚቻለውን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ለምክትል ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ አገራት ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በተለያዩ መሪዎች ደረጃ ጉብኝት መደረጉ ይታወቃል፤ በተጨማሪም በርካታባለሀብቶች መዋዕለነዋያቸውን አፍስሰው በአገራችን በግብርናና ቱሪዝም፤ እንዲሁም የተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ይገኛሉ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *