loading
ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ተመረጠች

አርትስ 06/03/2011
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል፡፡
አመሻሽ ላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሰሞኑን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት በፈቃዱ ራሱን ባገለለው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ቦታ በውክልና የፌደሬሽኑ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት የሆነችውን ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉን በፕሬዝዳንትነት ሰይሟል፡፡
በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት ለቀሪዎቹ ሁለት አመታት የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንት ያስመርጣል ሲል ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *