loading
ሚድሮክ ለዓመታት ከልሎ ያስቀመጣቸውን ቦታዎች አጥር ዛሬ ማፍረስ ይጀምራል

ሚድሮክ ለዓመታት ከልሎ ያስቀመጣቸውን ቦታዎች አጥር ዛሬ ማፍረስ ይጀምራል

አርትስ 12/03/2011

ፒያሳ አካባቢ ያለውን ስፍራ ለልማት ከተረከበ በኋላ ያለምንም ስራ ከ20 ዓመት በላይ አጥሮ ያስቀመጠው ሜድሮክ ኩባንያ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ለዓመታት ያለስራ ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን አጥር የማፍረስ ስራ ዛሬ በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል።

በመዲናዋ በተለያዩ አካባቢዎች በልማት ስም መሬት ከወሰዱ በኋላ ሳያለሙ ለበርካታ ዓመታት ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች ላይ ያሉ አጥሮችም ከነገ ጀምሮ እንደሚነሱም ተነግሯል።

የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ  ለረጅም ጊዜ አጥረው ከቆዩ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ንብረታቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባላነሱት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተከትሎ ነው አጥሮቹ የሚፈርሱት።

አስተዳደሩ ባልለሙ ቦታዎች ላይ ንብረቶቻቸውን ያስቀመጡ አካላት ንብረታቸውን እንዲያነሱ ከሳምንት በፊት መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

እንደ የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት ገለፃ ይሁን እንጅ እነዚህ አካላት ንብረቶቻቸውን ማንሳት ባለመጀመራቸው ምክንያት  ነው አስተዳደሩ ወደ እርምጃ የገባው ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *