loading
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ ባህርዳር ሊያቀኑ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ወደ ባህርዳር ሊያቀኑ ነው

አርትስ 12/03/2011

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና 300 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የፊታችን አርብ ወደባህርዳር ያመራሉ፡፡

 ከንቲባ ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ በከንቲባው የሚመራው የልዑካን ቡድን በሶስት ቀን የባህርዳር ቆይታው ብሄራዊ ሃብታችን የሆነውን ጣናን እየተፈታተነ ያለውን የእንቦጭ አረምን ያርማል ተብሏል፡፡

 የህዝብ ለህዝብ ውይይት ከከተማዋ ወጣቶች እና ከከተማዋ ኃላፊዎች ጋር ያደርጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሰል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች በቀጣይነትም ከኦሮሚያ  ከትግራይ እና ከሌሎችም የሃገሪቱ ከተሞች ጋር ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *