loading
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫቦርድ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሾሙ

ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫቦርድ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሾሙ

አርትስ 13/03/2011
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ማን ናቸዉ?
ወ/ሪት ብርቱካን የተወለዱት በአዲስ አበባ ሲሆን፤የመጀመርያ ዲግሪያቸዉን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ አግኝተዋል፡፡
ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን ደግሞ ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል፡፡ ወ/ሪት ብርቱካን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ፤ፖለቲከኛ ሁሉም ኢትጵያዊ በህግ ፊት እኩል መሆን አለብት ብለዉ የሚያምኑ ለዚህም መክፈል ያለባቸዉን መስዋዕትነት የከፈሉ ናቸዉ፡፡
ወ/ሪት ብርቱካን በፍርድቤቶች በዳኝነት ያገለገሉ ፤በኢትዮጵያ ምርጫ የተሳተፉ ፖለቲካ ፓርቲን በአመራርነት የመሩ ናቸዉ፡፡
በዉጭ ሀገር ናሽናል ኢንዶመንት ፎር ዲሞክራሲ በተባለ በምርጫና ዲሞክርሲ ላይ በሚሰራ ተቋም በምርጫና ዲሞክራሲ ጉዳይ ላይ ሰርተዋል፡፡
ዛሬ ደግሞ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነዉ ተሹመዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *