loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለወጣበት ብሔር ብሎ የሰረቀም የገረፈም የለም አሉ

አርትስ 18/03/2011

ጠቅላይ ሚኒስትር   አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ የህግ ተጠያቂነትን በተመለከተ ዶ/ር  አብይ በሚመጡ  ጥቆማዎች እንሰር ብንል ሌላስራ መስራት አንችልም፤ መፍትሄየሚሆነው ዋና ዋና የወንጀል ተዋናዮችናወደፊት እንዳንሄድ መሰናክል የሚሆኑብንንበመለየት የህግ ልዕልናን ማረጋገጥ ነውብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌላው ህግ እንዲከበርወይም ተፈፃሚ እንዲሆን በሚሰራበትወቅት አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ ሆኖየሚሰማን ከሆነ ወደ ምንፈልገውመምጣት አንችልም፤ ሰዎች እንደዛ አይነትአስተሳሰብ ሲያራምዱ ይሰማል፤ እንደዚህአይነት አስተሳሰብም በመንግስት በኩልየለም በእናንተም በኩል እንዲኖርአንፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ሁሉንም ከማሰር ይልቅ አብዛኛውን በጋራስምምነት ፋይል መዝጋትና ይቅር መባባልያስፈልጋል፤ በይቅርታ ብቻ የምንሻገረውመሆን አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡ እንደምሳሌም የሩዋንዳውን የዘር ፍጅትወንጀልንና የፍርድ ውሳኔውን በማነፃፀርአስረድተዋል፡፡

መንግስት በሰሞኑ እያደረገ ባለው የህግማስከበር  ሂደት ሰብአዊ መብት፣ ሙስና እናሆን ተብሎ የተደራጀ ሌብነት ላይ እንዳተኮረያስረዱ ሲሆን በሰብዓዊ መብት ጥሰትፖሊስና የደህንነት ተቋማት ተጠያቂዎችናቸው፤ አሁን ያለው ፖሊስ አንድ ቀንእንደሚጠየቅ ማወቅም ስላለበት ነው፤ኃላፊዎችም ቢሆኑ ከተለያዩ ብሄሮችየተወጣጡ ናቸው በማለት አክለዋል፡፡

ጥፋተኞች ሁሌም መደበቂያ ይፈልጋሉ፤ይሄም ይታወቃል፡፡ ከወንጀለኞቹ አንዱምለወጣበት ህዝብ ወይም ብሔር ብሎየሰረቀም፣ የገረፈም የለም፤ ምክንያቱምየወጣበት ብሔር መስረቅንም ሆነመግረፍን ስለማይፈቅድ ነው ብለዋል፡፡ ተጠያቂነት ሲረጋገጥም በዋና በደልፈፃሚዎች ላይ እንጅ በጅምላ አልተደረገምብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *