loading
ከንቲባ ታከለ ኡማ በፍትህ ስርዓቱ ላይ የከተማው አስፈፃሚ አካል አሉታዊ ተፅዕኖ አይኖረውም አሉ

አርትስ 20/03/2011

 

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ትናንት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ማዓዛ አሸናፊ ጋርተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

የውይይታቸው ትኩረት ከተማ አስተዳደሩ ከፍርድ ቤቱ ጋር የፍትህ የበላይነትንና የህግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በሚሰሩ የሪፎርምተግባራት ተባብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ነው ፡፡

ከከንቲባ ፅ/ቤት በተገኘው መረጃ ፍትህን ማረጋገጥ ልማትንና የህብረተሰብ ለውጥን ማረጋገጥ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩአስፈጻሚ አካል ምንም አይነት አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረውና ለህግ የበላይነት እንደሚሰራ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለሬዚዳንቷ አረጋግጠውላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *