loading
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመቆጣጠር እርምጃ መወሰድ ተጀመረ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመቆጣጠር እርምጃ መወሰድ ተጀመረ

አርትስ 26/03/2011

የኦሮሚያ ክልል ካቢኔ ግጭቱን ለማስቆም የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ እንደሚደግፍና ለተግባራዊነቱም እንደሚሰራ  አስታውቋል።

የክልሉ ካቢኔ ትናንት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ በዋናነት  በምእራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባጋጠመው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተወያይቷል።

የክልሉ ህዝብ የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን እያቀረበ ባለው ጥያቄ መሰረት በማድረግም እርምጃዎች መወሰድ ተጀምረዋል ። ይህም ተጠናክሮ  ይቀጥላል- እንደካቢኔው ውሳኔ።

እስካሁን በተወሰደው እርምጃም በዜጎች ላይ አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙ ከ200 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና የቀሩትንም በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ነው የተገለጸው።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ካቢኔው የፀጥታ ችግሩን ተከትሎ እየደረሰ ያለውን የሰው ህይወት መጥፋት እና የዜጎች መፈናቀል ለማቆም የብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ ገልጾ  ለተግባራዊነቱም ድጋፍ አደርጋለሁ ብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *