አዲሱ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የተናገርኩት ከሚጠፋ ብለው ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላናቸውን ገበያ አወጡ
አዲሱ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የተናገርኩት ከሚጠፋ ብለው ፕሬዝዳንታዊ አውሮፕላናቸውን ገበያ አወጡ
አርትስ 26/03/2011
የቀድሞው የሜክሲኮ ሲቲ ከንቲባ የነበሩት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ሜክሲኮን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ከተመረጡ ገና አንድ ሳምንት ኣልሞላቸውም፡፡
ታዲያ ፕሬዝዳንቱ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል ለመፈፀም ቀናት ብቻ በቂ እንደሆኑ በተግባር አሳይተዋል፡፡
ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶ ምርጫውን ካሸነፍኩ የፕዝዳንቱን ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ሸጨ እኔ ከህዝቤ ጋር እጓዛለሁ ብለው ነበር፡፡
በቃላቸው መሰረትም የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ይጠቀሙበት የነበረውን ኤርፎርስ ዋን አውሮፕላን እንዲሸጥ በይፋ ትዕዛዝ ሰጥተዋዋል፡፡
ኦብራዶር ሀገሬ በድህነት እየማቀቀች አኔ ግዙፍ አወሮፕለን ለብቻየ ይዠ ብቀናጣ አንገቴ በሀፍረት ይሰበራል እንጂ በህዝቤ ፊት ቀና ብየ መራመድ አልችልም ብለዋል፡፡
ሎፔዝ ኦብራዶር የፕሬዝዳንቱን ቢሮ በተረከቡ ማግስት ቬራክሩዝ ወደተባለቸው የሜክሲኮ የወደብ ከተማ ከህዝብ ጋር ተጋፍተው በንግድ አውሮፕላን ተጉዘዋል፡፡
እንደ አውሮፓያኑ አቆጣጠር በ2016 በ218.7 ሚሊዮን ዶላር የተገዛው የፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን ደግሞ ከመሸጡ በፊት ቴክኒካዊ ይዘቱ ሊፈተሸ ወደ ካሊፎርኒያ በሯል፡፡