እንግሊዛዊው ራሂም ስተርሊንግ ጋዜጦች ለጥቁር ተጫዋቾች በሚሰጡት ሰዕል ምክንያት ዘረኝት እንዲባባስ እያደረጉ ነው ሲል ተናገረ
እንግሊዛዊው ራሂም ስተርሊንግ ጋዜጦች ለጥቁር ተጫዋቾች በሚሰጡት ሰዕል ምክንያት ዘረኝት እንዲባባስ እያደረጉ ነው ሲል ተናገረ
አርትስ ስፖርት 30/03/2011
ተጫዋቹ ይሄን ያለው ቅዳሜ ዕለት በፕሪምየር ሊግ ክለቡ ማንችስተር ሲቲ በስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ከቼልሲ ጋር ሲጫወት በቼልሲ ደጋፊዎች የዘረኝነት ትንኮሳ ከደረሰበት በኋላ ነው፡፡ የ24 ዓመቱ ተጫዋች ኳሷን ከጎል ጀርባ ሊያመጣ በሚያመራበት ወቅት የተሰነዘረውን የዘረኝነት ዘለፋ ሁነት የምህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ተቀባብውታል፡፡
ቼልሲም በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን አጣርቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ቃል የገባ ሲሆን የከተማው ፖሊስ ስለ ኦንላይን የቪዲዮ ቅብብሎሹ እንደሚያውቅና ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ስተርሊንግ እኔ ማለት የምፍልገው በፍትሀዊነት እውቅና ላይ ሁለተኛ ሀሳብ አለኝ፤ አርሱም ለሁሉም ተጫዋቾች እኩል ዕድል ይሰጥ ነው ብሏል፡፡
ተጫዋቹ በኢንስታግራም ገፁ እንዳሰፈረው በጨዋታው መሀል የዘርኝት ትንኮሳው ሲሰነዘርበት እንደሳቀና ከዚህ የተሻለ ልጠብቅ አልችልምና ሲል ተናግሯል፡፡