ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ‘ኢንዴንጀር ሄልዝ’ ተቋም ን አነጋገሩ
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የ‘ኢንዴንጀር ሄልዝ’ ተቋም ን አነጋገሩ
አርትስ 3/04/11
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በጤናማ ስነ–ጾታና ስነ–ተዋልዶ ዙሪያ የሚሰራውን የ‘ኢንዴንጀር ሄልዝ’ ተቋም ፕሬዚዳንት በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡
የተቋሙ ፕሬዚዳንት ትሬሲ ኤል ቤይርድን ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ድርጅቱ በአማራ ክልል ውስጥ ሞዴል የቤተሰብ ምጣኔ ላይ ያተኮረ ስራ በማከናወን የሚያበረታታ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸውላቸዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሴቶች በጾታ ልዩነት ሳይገደቡ መብታቸውን እንዲያስከብሩና በሚመለከታቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዲችሉ ድርጅታችን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋቸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ በበኩላቸው ወጣት ሴቶች በተለይ በትምህርት ወቅት በሁለንተናዊ መልኩ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ ተቋሙ ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እንዲያከናውን ፕሬዚዳንቷ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ፡፡ መረጃው የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ነው፡፡