loading
ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በድንበር አካባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶችና መከላከያ መንገዶቻቸው ላይ መከሩ

ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በድንበር አካባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶችና መከላከያ መንገዶቻቸው ላይ መከሩ

አርትስ 05/04/2011

 በሃዋሳ ከተማ በተካሄደውና በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወሰን አካባቢ ከጋራ ሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት በመከረው በዚሁ መድረክ ላይ ሃገራቱ ችግሮችን በመፍታት  ዘላቂ ሰላም ማስፈን አለባቸው ተብሏል።

በዚሁ በሁለቱ ሃገራት የወሰን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ምክክር ላይ ከሁለቱ ሀገራት የተወከሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል እንደገለጹት የኢትዮጵያና የኬኒያ መልካም ጉርብትና በአፍሪካ በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው ።

አልፎ አልፎ በሁለቱ ሀገራት ወሰን አካባቢ ከሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተለመዱ ግጭቶች መኖራቸውን እና የውይይት መድረኩ ችግሮችን እንደ ባህላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶች ባሉ ዘዴዎች ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ተናግረዋል።

ለዚህም ቀደም ሲል በደቡብ ኦሞና ቱርካና ሃይቅ፣ በኢትዮጵያና ኬኒያ ሁለቱም ሞያሌዎች አካባቢ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦችን ያሳተፉ ተመሳሳይ ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *