loading
በአዲስ አበባ የተገኙት 7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች ንብረትነታቸው የቀድሞ ኪራይ ቤቶች የአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ነዉ ተባለ

አርትስ /08/04/2011

በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ዝናቡ ቱኑ ለአርትስ እንደተናገሩት ከ7ቱ ድብቅ እስር ቤቶች መካከል የሚደረግባቸው ምርመራ ተጠናቆ የተወሰኑት ለቤቶች ኮርፖሬሽን ተመልሰዋል፡፡

አቶ ዝናቡ ቦታዎቹ የት እንደሆኑ  በቅርቡ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እናደርጋለን ብለዉናል፡፡

ዜጎች የተለያየ ስቃይ እና እንግልትን አሳልፈውባቸዋል የተባሉት እነዚህ ድብቅ እስር ቤቶች በቀድሞው የኪራይ ቤቶች ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በአሁኑ የቤቶች ኮርፖሬሽን ሲተዳደሩ እንደቆዩ ተረጋግጧል ፡፡

የቀሩት ግን የሚደረግባቸው ምርመራ ስላላለቀ ታሽገው እንደሚገኙ ከአቶ ዝናቡ ሰምተናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *