loading
ኦዲፒ የጥፋት ሀይሎችን ሴራ አክሽፌ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥ ማንኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ ወስኛለሁ አለ

አርትስ ታህሳስ 12 2011

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በወቅታዊ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይስብሰባ በማድረግ ውሳኔ ባሳለፈበት ወቅት ነው ይህ  የተገለጸው ።

በውሳኔው ፓርቲው የጥፋት ሀይሎች በተቀናጀ መንገድ የሚሸርቡትን ሴራ አክሽፎ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥማንኛውንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑን አስታውቋል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዳር እስከ ዳር በፖለቲካ ነፃ የወጣውን ህዝብ በኢኮኖሚምነፃ ለማውጣት እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት በሰላማዊ መንገድ ትግል ለማድረግ የተገባው ቃል ፈርሷል ብሏል።

ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ያሳየውን ትዕግስት እንደ ፍራቻ የቆጠሩ ከስልጣን የተባረሩ አካላት ተላላኪዎችን በመግዛትኦሮሚያን እና ኦሮሞን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየሰሩ ነው ብሏል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መግለጫ ።

እርስ መዋጋት እና መታኮስ ወደ ቀጣይ ምእራፍ አያሻግረንም ያለው መግለጫው እኛ ከተጋጨን በመሃል ህዝቡ ይጎዳልበሚል ታግሰን ቆይተናል ነው ያለው።

ነገር ግን ጥፋቱ ከዚህ በላይ ከቀጠለ የህዝብ እልቂት እና የሀገር መበተንን ያስከትላልም ነው ያለው።

ስለሆነም ኦዲፒ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ጠላቱን አሸንፎ የህግ የበላይነትን እና የህዝብን ሰላም ያረጋግጣል ያለው መግለጫው በሚወስደው እርምጃም የኦሮሞ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *